EqubBook · ዕቁብ ደብተር
ግባ
ባህላዊ ዕቁብ · ዲጂታል እምነት

ዕቁብዎን በወረቀት ሳይሆን በስልክ ያስተዳድሩ።

ማን እንደከፈለ፣ ማን እንደቀረ፣ ዕጣ ለማን እንደወጣ — ሁሉም በግልጽ፣ ሁሉም አባላት በስልካቸው ያያሉ። ክርክርና ጥርጣሬ ይቀራል።

ለምን EqubBook?

📒
የጠፋ ደብተር የለምእያንዳንዱ ክፍያ በግብይት ቁጥሩ ይመዘገባል። ሊሰረዝ አይችልም። ሙሉውን መዝገብ በExcel ያውርዱ ወይም በPDF ያትሙ።
🎲
ፍትሐዊ ዕጣዕጣው ሁሉም አባላት በሚያዩት መንገድ ይወጣል። አንድ ዙር አንድ ጊዜ ብቻ — ማንም ሊደግመው አይችልም።
📣
ማስታወሻ በአንድ ንክኪላልከፈሉ አባላት በቴሌግራም ወይም በዋትስአፕ ማስታወሻ ይላኩ።
👀
ሁሉም ያያልእያንዳንዱ አባል የዙሩን ሁኔታ፣ የክፍያ ታሪክና አሸናፊዎችን ከስልኩ ያያል።
🔒
ገንዘብ አንይዝምአባላት በቀጥታ ለሰብሳቢው ይከፍላሉ። EqubBook መዝገብ ብቻ ነው።
📱
በማንኛውም ስልክበብራውዘር ይሰራል፣ እንደ አፕም ይጫናል። በአማርኛና በእንግሊዝኛ።

📲 EqubBookን እንደ አፕ ይጫኑ

አንድሮይድ፦ /app ን በክሮም ይክፈቱ → «አፕ ጫን» ይንኩ (ወይም ⋮ → Install app)።
አይፎን፦ በሳፋሪ ይክፈቱ → Share ⬆️ → «Add to Home Screen»።
ከአፕ ስቶር ማውረድ አያስፈልግም፤ ትንሽ ነው፤ ሁልጊዜ የቅርብ ጊዜውን ስሪት ያገኛሉ።
አፑን ክፈት

እንዴት ይሰራል?

ሰብሳቢው ዕቁብ ይፈጥራል — ስም፣ መዋጮ፣ የአባላት ብዛትና ቀን። ባለ 6 ፊደል ኮድ ያገኛል።
አባላት በኮዱ ይቀላቀላሉ — ሊንኩን በቴሌግራም ይልካል፤ ሰብሳቢው ያጸድቃል።
አባላት ይከፍላሉ — በቴሌብር ወይም በባንክ ለሰብሳቢው ከፍለው የግብይት ቁጥሩን ያስገባሉ። ሰብሳቢው ያረጋግጣል።
ዕጣ ይወጣል — ሁሉም ሲከፍሉ ሰብሳቢው ዕጣውን ያወጣል፤ ሁሉም አባላት አሸናፊውን በቀጥታ ያያሉ።

ዋጋ

ለሰብሳቢው
ከ150 ብር ጀምሮ
በወር · ለአባላት ነፃ · የመጀመሪያው ወር (30 ቀን) ነፃ
እስከ 15 አባላት፦ 150 ብር · እስከ 40፦ 300 ብር · እስከ 200፦ 600 ብር
ዓመታዊ ሲከፍሉ 2 ወር ነፃ
ነፃ ይጀምሩ

🛡️ እምነትና ደህንነት — ጥያቄና መልስ

ሰብሳቢው መለያውን ቢያጣስ?

በGoogle የገቡ በGoogle ይመለሳሉ። መረጃው በስልኩ ሳይሆን በደመና ላይ ስለሚቀመጥ ስልክ ቢጠፋም ምንም አይጠፋም። በአዲስ ስልክ ገብተው ይቀጥላሉ። በስልክ ቁጥርና ፒን የሚገቡ ሰብሳቢዎች ፒናቸውን ጽፈው በጥንቃቄ ያስቀምጡ፤ ለሰብሳቢዎች በGoogle መግባትን እንመክራለን።

አባል የራሱን ክፍያ ማረጋገጥ ይችላል?

አዎ። እያንዳንዱ አባል በ«ታሪክ» ውስጥ የራሱን የአባላት መግለጫ፣ የከፈላቸውን ዙሮች፣ ያልከፈላቸውን ዙሮችና የሁሉንም ክፍያ መዝገብ ያያል።

ዕጣው ፍትሐዊ መሆኑን እንዴት እናውቃለን?

ዕጣው ደህንነቱ በተጠበቀ የዘፈቀደ ቁጥር ይወጣል። ቁጥሩና የተወዳዳሪዎቹ ዝርዝር ተመዝግበው ይቀመጣሉ፤ ማንም አባል «ማረጋገጫ»ውን አይቶ ሂሳቡን ራሱ መፈተሽ ይችላል። አንድ ዙር አንድ ጊዜ ብቻ ይወጣል፤ ማንም ሊደግመውም ሊቀይረውም አይችልም።

የተሳሳተ የግብይት ቁጥር ቢገባስ?

ሰብሳቢው «አልደረሰም» ይላል። የመጀመሪያው መዝገብ አይሰረዝም፤ ታሪክ ውስጥ ይቀራል። አባሉ በትክክለኛው ቁጥር እንደገና ያስገባል።

ሙሉውን ታሪክ ማውጣት ይቻላል?

አዎ። ማንኛውም አባል በአንድ ንክኪ ሙሉውን መዝገብ በExcel (CSV) ያወርዳል ወይም እንደ PDF ያትማል። በወረቀት የሚፈልጉ አባላትም ታትሞ ሊሰጣቸው ይችላል።

የአባላት መረጃ እንዴት ይጠበቃል?

የዕቁቡን መረጃ የሚያዩት የዕቁቡ አባላት ብቻ ናቸው። የአባላት ስልክ ቁጥር የሚያየው ሰብሳቢው ብቻ ነው። መረጃው በGoogle Firebase ደህንነቱ በተጠበቀ አገልግሎት ላይ ይቀመጣል።

አገልግሎቱ ቢቋረጥ መዝገቡ ይጠፋል?

አይጠፋም። መረጃው በGoogle ደመና በብዙ ቦታ ተቀምጧል። በተጨማሪም ማንኛውም አባል በማንኛውም ጊዜ ቅጂውን አውርዶ ማስቀመጥ ይችላል።

ምዝገባ ካልከፈልንስ? ታሪኩ ይጠፋል?

በፍጹም አይጠፋም። ምዝገባው ሲያበቃ አዲስ ክፍያ መመዝገብና ዕጣ ማውጣት ብቻ ለጊዜው ይቆማሉ። ሁሉም አባላት የቆየውን ታሪክ ማየት፣ ማውረድና ማተም ይቀጥላሉ።

ማሳሰቢያ፦ EqubBook ገንዘብ አይቀበልም፣ አይይዝም፣ አያስተላልፍም። ገንዘቡ ከአባላት በቀጥታ ወደ ሰብሳቢው ይሄዳል። EqubBook የዕቁቡን መዝገብ ብቻ ይይዛል። የዕቁቡ ኃላፊነት የሰብሳቢውና የአባላቱ ነው።